ዩጋንዳ የቡና ምርቷን ለመጨመር አቀደች

ሁለተኛዋ የአፍሪካ ቡና ላኪ የሆነችው ዩጋንዳ በ2025 ከአለም ሶስተኛዋ ትልቁ ቡና ላኪ ለመሆን የጀመረችውን ታላቅ ዘመቻ እንደገና ጀምራለች። እቅዱ ሀገሪቷ በ2020 ወደ 6 ሚሊየን የሚጠጉ 60 ኪሎ ከረጢቶችን ወደ አለም ገበያ ከላከች በኋላ ነው።

በእቅዱም አርሶ አደሮች እንዲመዘገቡ እና ደረጃዎች እንዲከበሩ የሚያዝ አዲስ ህግ ፤ አሮጌ የቡና ዛፎችን በአዲስ ዛፎች በመተካት ግቡን ለማሳካት ከተቀመጡ የእርምጃዎቹ መሃል ናቸው። በያዝነው የምርት ዘመን አመት ከ8 ሚሊየን ከረጢት ምርት ውስጥ 6 ነጥብ 5 ሚሊየን ከረጢት ኤክስፖርት ለማድረግ አቅዳ በመስራትም ላይ ትገኛለች።
እ.ኤ.አ. በ 1990 ዎቹ ውስጥ በሮቡስታ የቡና ዛፎች ላይ በተከሰቱ የቫይረስ ኢንፌክሽኖች ምክንያት የቡና ምርት ከቀነሰ በኋላ የኡጋንዳ ሳይንቲስቶች በሽታን የመቋቋም ችሎታ ያላቸው አዳዲስ ዝርያዎችን በማራባት ወደቀድሞ የምርት ደረጃዎች ለመመለስ ችለዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የቡና ​​እርባታ እመርታን በማሳየት ቡና የኡጋንዳ ዋነኛ ገንዘብ አምጪ በመሆን ለአፍሪካዊቷ ሀገር ሁለተኛው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ አስመዝግቧል።

leave a reply